የለም ያሉት
የሉም
ዛሬ መስከረም 2 ነው፡፡ አይ መስከረም ሁለት ያለው ግርግር የኢትዮጲያዊነት
ወኔ ቀስቃሽ ኢትዮጲያ ትቅደም ፣ ሽለላ፣ ፉከራ፣ቀረርቶ፣ የሰልፈ ትርኢትና ዳንኪራ፣ ዘፍንና ጭፈራ አጠቃላይ የነበረው ፈንጠዝያን
ለተመለከተ ጌታን በደመና ለመቀበል በደስታ እየተጠባበቁ ያሉ የሚነጠቁ ነፍሳትን ሊመስል እብዛም አይቀርም ነበር ፡፡
በቃ ህይወት እንደዚህ ናት አንዱ ይሔዳል ሌላው ይመጣል ድግግሞሽ፣ ፍርርቆሽ
፣ እሽቅድምድሞሽ … የጨለማ ካባውን ደርቦ የመብረቅ ሳቅ እየሳቀ አሰስ ገሰሱን ለብሶ ጳጉሜን ከጠቀለት በኃላ አሮጌውን ዘመን እብስ
አለ፡፡ ምንም ቋሜ ነገር የለም የሚያሳልፋቸው፣ የሚኖራቸው የሚቆጣጠራቸው
ብቻ ፤፤መላ ኢትዮጲያን ያጥለቀለቀው የ66ቱ አቢዮት በተማሪና ገበሬ አመጽ ተጀምሮ ወታደራዊ ነውጦችን አሰከትሎ መለኮታዊ
ነኝ ብሎ የሚያስበውን የአፄውን መንግስት ባፍጢሙ ደፍቶ መቀመቅ ካወረደ በኃላ
ሀገሪቱን ሀገር ለመምራት እውቀትም ዝግጅትም ለሌላቸው ራሳቸውን ደርግ ብለው ለሰየሙ መቶ ሃያ ወታደሮችን ላቀፈ ጁንታ አሳልፎ ሰጠ፡፡
ፍቅረ ስላሴ ወግደረስ እንደሚሉት ተማሪው የምንመራበትና ሪዕዮተ-ዓለም ይታወቅ ስላለና ኢትዮጲያ ውስጥ በአብዛኛው በጊዜው ሁሉም
ሰው ገብቶትም ይሁን ሳይገባው ስለ ሶሻሊዝም አብዝቶ ያወራ ስለ ነበር አንድ ቀን ጧት ከእንቅልፋቸው እንደተነሱ አንድ ስብሰባ ጠርተው
በቃ ሶሻሊስት እንሁን አንሁን ብለው ሶሻሊስትን ከወደ ራሽያና ኩባ አስመጥተው ሶሻሊስት ሆነው አረፍት ፡፡
በጽንሰ
ሀሳብ ደረጃ ህብረተሰባዊነት መጥፎ ነው ላይሆን ይችላል ዋና ነገር ግን የተኛውም አይነት አስተሳሰብ የህብረተሰቡን እምነት፣ታሪክ፣ባህል፣ሃይማኖት፣
እሴት አጠቃላይ ማህበረሰቡ የተመሰረተበትን ስሪት ማክበር አለበት ፡፡ ይኽ ደግሞ ህብረተሰባዊ ነኝ ብሎ ከሚያስብ የበለጠ ይጠበቃል
፡፡ በጊዜው እየሆነ የነበረውና እንደ ተራማጅ ስልጡን ያስቆጥር የነብረው ግን ካኪ ጨርቅ እየቀያየሩ ግራ እጅን እያወናጨፉ እግዚአብሔር
የለም ማለት ነበር ፡፡
የእግዚአብሔርን ህልውና ማንም ሰው ተገዶ እንዲቀበል ይደረግ እያልኩ አይደለም
፤ እግዚአብሔር ማንንም አስገድዶ የገዛበት ጊዜ አልነበረም አይኖርምም ፡፡ በግድ ልንጭንበት ብንፈልግ እንኴን ሃይል ባገኘ አቅም
ባጠነከረ ገዜ የተጫነበትን ሸክም አሽቀንጭሮ መጣሉ አይቀርም ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በግድ ማንም እግዚአብሔርን ከማመን ማንም ሊከለክል
አይችልም ነፃነት በነፃነት እንድንኖር ከሰጠን ከእግዚአብሔር የተገኘ ነውና ፡፡በመፎክር ብዛትም የእግዚአብሔርን ህልዉና ልናስቀረው
አንችልም ፤፤እምነት ደግሞ የልብ ነው፡፡ አዋጅ በሚመስል ሁኔታ በማስፈራራትና በማግለል አንድ ሰው የሚያምንበትን እየደፈጠጡ የራስን
አመለካከት ለመጫን ሲሞከር ግን ማንም ሰው ነፃነቱን መፈለጉ አይቀርምና የፍላጎት ልዩነት ይፈጠራል ይህ ልዬነት አድጎ አድጎ ሊፈታ
ወደማይችል ቅራኔ ያድግና ፍጹም ደም አፋሳሽ የሆነ ጥፋት ሊሸጋገር የችላል ያኔም የሆነው ይሄው ነው ፡፡
በጊዜው የስቃዩና የመከራው ብዛት አሰቃቂ ቢሆንም እግዚአብሔር በወንጌል እሳት
ልባቸውን ያቀለው ምዕመናን እግዚአብሔር አለ ብለው በስሙ አምነው ሞተዋል ፡፡ የተገረፉና አካለ ጎደሎ የሆኑ ብዙ ናቸው ፡፡ ቤተክርስቲያን መሄድ እንደነውር
የሚቆጠርበት መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ መገኘት ህገ መንግስትን እንደመናድ የሚታይበት የትኛውም አይነት የሃይማኖት እንቅስቃሴ በአይነ ቁራኛ የሚታይበት
ዘግናኝ ዘመን ነበር ፡፡የአትዮጵያ ቤተክርስቲን ደግሞ ዋና ገፈት ቀማሽ ነበረች ሌላውን እንኳን ብንተወው ሁለተኛውን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ
አቡነ ቴዎፍሎስን በሞት ስታጣ ብጹዕ አብነ ጳውሎስን ብኋላ አምስተናው ፓትርያርክ የሆኑ ሰምንት አመት በግዞት እንዲሰቃዩ ተፈርዶባቸዋል፤፤
መጽሐፍ ቀን የሚያመጣውን አታውቅምና ነገ በሚሆነው ነገር አትመካ እንዲል ደግሞ
ዘመን መጣ ፡፡ መስከረም ሁለትም ከዚያ ሁሉ ድንፋታውና ትዕቢቱ ጋር ወዴት እንደሄደ እንኳን ሳጥታወቅ ስማጠራሩ ጠፋ ፡፡ ዛሬ መስከረም
ሁለት ነው እንደገና ላስታውሳችሁ ወጣ ብላችሁ ቃየውን ፣ አደባባዩን
፣ አውራ ጎዳናውን እዩት ፀጥ ረጭ ብሏል ምንም የለም ፡፡ እግዚአብሔር የለም ያሉትም የሉም ፡፡
ማንም ይሁን ማን አሁን ያለነውም ይሁን ወደ ፊት የሚመጡት ከባለፈው የውድቀታችንና
የመከራ ዘመናችን ብዙ ልንማር ይገባናል ፡፡ ከእግዚአብሔር በራቅን ቁጥር ብዙ ተጎድታል ፣ ሀገር ፈርሷል፣ ትውልድ ጠፍቷል ፤ ቀይና
ነጭ እያልን እርስ በእርሳችን ተራርደናል ፣ በርሃብ አለንጋ ተገርፈን የችጋር ምሳሌ ሆነን ቀርተናል ፡፡ ጉልበተኛ ብቻ የሚኖርባት ሃገር ፈጥረናል ፡፡
እነዚህ ሁሉ ውርደቶቻችን ናቸው ፡፡ ከመስከረም ሁለት ጋር አብረው መጥፋት ያለባቸው መልሰን አሁንም ደግመን በዚሁ መንገድ የምንሔድበት
ከሆነ ግን ያው የተዘራ መብቀሉ አይቀርም ፤ የዘራነውን እናጭድና የመከራ ቋት እንደሆንን እንቀጥላለን ፤ ቤተ መንግስቱም ቤተ ክህነቱም
ሌላውም ሁላችንም በቃ ያለፈው ይብቃን ፡፡
ወደ መሰረታዊ
ነገራችን እንመለስና እስኪ ጥያቄ እናንሳ፤- እንደው ግን እግዚአብሔር ስለሌላ ነው ወይ የለም ያሉት? ግን በርግጥስ አለ ወይ? ማረጋገጫውስ ምንድን ነው
?
ይቀጥላል …….
የእግዚአብሔር ፀጋ ምድርን ሁሉ የሚከድበት ዘመን ይሁን፤፤ ለዓለም ሁሉ ሰላም
፤፤
መስከረም 2› 2007 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment