የመጀመሪያይቱ የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት
በቆሮንቶስ ላለችው የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን
መግቢያ
v
የቆሮንቶስ
ከተማ
መልክዓ ምድር:
·
ከግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ 75 ኪ.ሜ ትርቃለች
·
በሁለቱ የግሪክ ጠቅላይ ግዛቶች /አኪያና መቅዶኒያ/ መካከል ባለው ልሳነ ምድር ላይ የተገነባች
ከተማ ነበረች
·
የአካያ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማም ነበረች
·
የሮማው ምክትል ቆንሲል መቀመጫም ስለነበረች ብዙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ነበሩባት
1.
ንግድ :
·
በብዙ የባሕር ወደቦች የተከበበች ከተማ በመሆኗ ከልዩ ልዩ የዓለም ክፍል የተሰበሰቡ ነጋዴዎች በከተማዋ ይኖሩ ነበር። በዚህም ታላቅ የንግድ ማዕከል ሆነች
·
ከሮም ወደ ምስራቅ ለሚደረገው ታላቅ የንግድ ጉዞ ሁነኛ የባሕርይ መሸጋገሪያ ነበረች
·
ከብልጥግናዋ እና ከስልጣኔዋ የተነሣ እጅግ የከፋ ኃጢአት የሚደረግባት ከተማ ሆነች። ከዚህ የተነሣ ቆሮንቶሳዊ መሆን የእፍረት
ምክንያት እስከመሆን ደርሶ ነበር።
·
ቆሮንቶስ በራዕይ ዮሐንስ ላይ የተጠቀሰችውን ባቢሎን
እስክመምስል ደርሳ ነበር ራዕ 18፥2፤ ራዕ 17፥5
2.
ሃይማኖት :
·
የተለያዩ ሃይማኖቶች የአይሁድ እምነትን ጨምሮ በከተማዋ ነበሩ
·
ከ20 በላይ የጣዖት መቅደሶችም ነበሩባት
·
የአይሁድ ምኩራብም እንዲሁ በዚያው ነበር ሐዋ 18፥1
·
አፍሮዲቴና leእርሷ የተቀደሱ 1000 ሴተኛ አዳሪዎች
ነበሩ ሮሜ 1፥26
3.
ማኅበራዊ እንቅስቃሴ :
·
ከንግድ ከተማነቷ ጋር ተያይዞ ስፖርት፣ ቲያትር እና ሥነጥበብ በቆሮንቶስ ይዘወተሩ ነበር
·
ሮማውያን፣ አይሁዶችና ግሪኮች የሚኖሩባት ከተማ
በመሆኗ ማኅበራዊ እንቅስቃሴውና ባሕሉ ቅይጥ ነበር
·
አብዛኛዎቹ ነዋሪዎችና ነጋዴዎች ግሪኮች ስለነበሩ
የከተማዋ የሥራ ቋንቋ ግሪክኛ ነበር
·
ሐዲስ ኪዳን ወደ አሕዛብ ምድር ከገባበት ዘመን
600 ሺህ ሕዝብ የሚኖርባት ታላቅ ከተማ ነበረች።
v የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን
·
በሐዋርያው ጳውሎስ ሁለተኛ የወንጌል ጉዞ ተመሰረተች።
ሐዋ 15፥36፤ 16፥6
·
ጊዜው ከ50-52 ዓ.ም ሲሆን በዚህ ወቅት ጳውሎስ
በቆሮንቶስ ከአንድ ዓመት ከስምንት ወር በላይ ተቀምጧል።
·
በምኩራብም ተሳዳቢዎች ስለበዙ ያመኑትን ነፍሳት
ለይቶ በአንድ ግለሰብ ቤት በማስተማር አገልግሎቱን ጀምሯል ሐዋ
18፥6
v የቆሮንቶስ ክርስትና
·
ለፍጹማን እንኳን ፈታኝ የሆነ ትግል ውስጥ ነበረች
·
የቆሮንቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብታ ነበር
·
አብዛኞቹ ድሆችና ጥቂት ባለጠጎች የነበሯት ቤተክርስቲያን
በመሆኗ ቆሮንቶሳዊneት /መለያየት/ ገላ 5፥21 ለተባለው ኃጢአት
ተላልፈው እንዲሰጡ ይህንን ሰይጣን እንደ ልዩነት ምክንያት ያሳያቸው ነበር፡- የአጵሎስ፣ የጳውሎስ፣ የኬፋ፣ የክርስቶስ በመባባል
·
በአሕዛብ መካከል በቁጥር ትንሽ ስለነበሩ እጅግ
ይጨነቁ ነበር 2ቆሮ 2፥7
·
ጋብቻ መፈጸምና፣ ለጣዖት ያልተሰዋ ሥጋ ማግኘት
እንኳን ከባድ ነበር::
v መልዕክቱ የተጻፈበት ምክንያት:
1.
በቤተክርስቲያኒቱ ኃጢአትና ርኩሰት (ዝሙት 1ቆሮ 5፥1 ፤ መለያየት 1ቆሮ 1፥11 ፤ መፈራረድ 1ቆሮ 6፥1 ፤ ለጌታ ክብር አለመሰጠት 1ቆሮ
11፥1 )ስለበዛ ተግሳጽና ምክር ለመስጠት
2.
ሃይማኖታዊ ክርክሮችና ጥያቄዎች ስለበዙ መልስ ለመስጠት
·
ስለ ትንሳኤ ሙታን 1ቆሮ 15፥1 እስከ ፍጻሜው
·
ስለጌታ ራት 1ቆሮ 11፥1-16
·
ስለ ጋብቻ 1ቆሮ
7፥1 እስከ ፍጻሜው
·
በመንፈስ (በጽድቅ) ስለማደግ 1ቆሮ 3፥1-5
v የመልዕክቱ ዋና ሐሳብ
·
በቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተነሳውን ማዕበል
ማቆም
·
ቅርጽ ያለው የቤተክርስቲያን አደረጃጀት መፍጠር
·
ቤተክርስቲያኒቱን ወደ ውበቷ መመለስ
·
አማኞችን ከአባልነት ወደ አካልነት ማሳደግ
·
ከእጮኝነትም አልፈው ለሚስትነት እንዲዘጋጁ ማድረግ
v የመልዕክቱ ጸሐፊ : - ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
-
መንፈስ ቅዱስ
·
የጻፈው በኤፌሶን ተቀምጦ ሳለ ከ55-56 ዓ. ም ባለው ነው።
የመምህር በሪሁን ገጽ: የመጀመሪያይቱ የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት በቆሮንቶስ ላለችው የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን መግቢያ >>>>> Download Now
ReplyDelete>>>>> Download Full
የመምህር በሪሁን ገጽ: የመጀመሪያይቱ የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት በቆሮንቶስ ላለችው የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን መግቢያ >>>>> Download LINK
>>>>> Download Now
የመምህር በሪሁን ገጽ: የመጀመሪያይቱ የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት በቆሮንቶስ ላለችው የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን መግቢያ >>>>> Download Full
>>>>> Download LINK