Monday, July 8, 2013

ዮሐንስ ራዕይ

እንደ መግቢያ፤-

አንዳንድ ሊቃውንት ዮሐንስ ራዕይ የሚተረጎመው ዘመኑ ሲደርስ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ የለም ጌታ ሁሉን ነግሮናል መንፈስ ቅዱስን አጋዥ አድርገን እንተረጉመዋለን ይላሉ፡፡የተቀሩት ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ አስተማሪነት እንዳለ ሆኖ ዘመን የሚገልጠው ነገር አለ ፤ በተፈሮ ሁኔታ የሚፈታ አለ፤በዓለም ተለዋወጭ ሁኔታ(በሳይንስና ቴክኖሎጅ ፤ በስነ-ምግባርና በሞራል ጉዳዮች…..) እና በአጠቃላይ ከዕለት ዕለት የሰው ልጅ እንቃስቃሴ ጋር ተያይዞ የሚተረጎም አለ ይላሉ፡፡ የሆነ ሆኖ እኛ ግን የቆየውን የኢትዮጵያ ሊቃውንት አስተምህሮ እየተከተልን ነገሩን ለመመርመር እንሞክራለን፡፡

ጌታችን ሁሉን ከፈጸመ ብኃላ አጽናኙን አንደሚልክላቸው ለሐዋርያቱ ቃል ገብቶ የነፋስ መሰላል የአየር መወጣጫ ሰርቶ ደመናውን እየረገጠ ወደ ሰማይ ወጣ፡፡ በጊዜው የነበሩት መላእከት ደገሞ የመንፈስ ቀዱስ መውረድ በቻ ሳይሆን ኢየሱስም ተመልሶ እንደሚመጣ አበሰራቸው፡፡ ደስታቸውም እጽፍ ድርብ ሆነ፡: በዚህም እሰከ ዓለም ፍጻሜ ከእናንተ ጋር ነኘ ያለው የመጽሐፍ ቃል ተፈጸመ፡፡

በሃይማኖት ስንኖር ነፍሳችንን አስይዘን ቢሆን ከምንወራረድባቸው ጉዳች አንዱ የጌታ ዳግም ምጽአት ነው፡፡ በእርግጥ ጌታ ይመጣል፡፡ አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል።  አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥    ራዕ 2220 በሌሎች ገጸ-ምንባባትም እንዲህ ተጽፎል:-

የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤ መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ። ማቴ 2430-31

እግዚአብሔር እንዴህ ይላል በጫንቃ ላይ ይሸከሙአችኋል በጕልበትም ላይ እያስቀመጡ ያቀማጥሉአችኋል።
እናት ልጅዋን እንደምታጽናና እንዲሁ አጽናናችኋለሁ፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ትጽናናላችሁ  ኢሳ 6612-13


ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ። ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤ ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው። የሐ 18-11

     ሊሆን ያለውን ሁሉ ግን ጌታ ኢየሱስ አስቀድሞ በማቴዎስ ወንጌል 241-ፍም እንደተጻፈው በዝርዘር ከነምሳሌውና ምልክቱ ገልጦላቸዋል፡፡ ይህ ክፍል ለዮሐንስ ራዕይ እንደመግቢያ ነው ብየ አስባለሁ ወይም ዮሐንስ ራዕይ የዚህ ክፍል ዝርዘር ትርጉም ነው እንደማለት ነው፡፡ ነገረ ምጽዐትን የሚተርከውን ይህንን ምዕራፍ በአራት ዓበይት ክፍሎች ልንከፍለው እንችላለን፡፡

1.    በእስራኤል የሚከሰቱ ሁኔታወች
2.    በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚፈጠሩ ነገሮች
3.    ተፈጥሮዊ ኩነቶች
4.    ሃይማኖተዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡

………. ይቀጥላል………

1 comment:

  1. የመምህር በሪሁን ገጽ: ዮሐንስ ራዕይ >>>>> Download Now

    >>>>> Download Full

    የመምህር በሪሁን ገጽ: ዮሐንስ ራዕይ >>>>> Download LINK

    >>>>> Download Now

    የመምህር በሪሁን ገጽ: ዮሐንስ ራዕይ >>>>> Download Full

    >>>>> Download LINK

    ReplyDelete