Monday, July 15, 2013

ዮሐንስ ራዕይ

ክፍል ሁለት

ይሄው ዓለምም ሳትጠፋ የፈረንጆቹ Dec 21-2012 አለፈ፡፡ እግዚአብሔርም ዘመን ለንስሀ ጨመረልንና እንደገና ተገናኘን እንዴት ሰነበታችሁ ዘመዶቸ፤፤ወደፊት በዝርዘር የምንመጣበት ቢሆንም ከዓለም ጥፋት ጋር ተያይዞ አንድ ሁለት ነገሮችን ጠቆም ላድርግና ወደዛሬው ክፍል ልለፍ፡፡
1.      ከዓለም ጥፋት በፊት አውሬው (የጥፋት ልጅ) በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ይቀመጣል:: ይህ ማለት ደግሞ እስራኤል 3ውን    ቤተ መቅደስ ሳትስራ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት አይሆንም ማለት ነው፡፡
2.      ከዚህ በፊት ዓለም ጠፍቶ ያውቃል (በኖህ ዘመን) ታዲያ ያኔ እግዚአብሔር ምርጦቹን ከጥፋት ከለላቸው፡፡ ስለዚ ዓለም ቢያልፍም ባያልፍም ፤ በማነኛውም ጊዜ እና ሁኔታ እግዚአብሔር ልጆቹን ይጠብቃል::
አሁን ደግሞ ወደ ዛሬው ትምህርታችን እንመለስ
ስለ ፍጻሜ ዘመን ስናስብ በቅድስቲቱ ከተማ በተቀደሰው ቤተ መቅደስ በቅዱሱ ህዝብ በአጠቃላይ በቅድስት ሀገር የሚከሰቱት ኩነቶች እጅግ ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ወሳኘ ጉዳዮች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ጌታም እንደተናገረው እነዚህ ነገሮች በስስራኤል ይሆናሉ :-
1.       ድንጋይ በዱንጋይ ላይ ይፈርሳል
2.       በለሷ ትለመልማለች
3.       አንድ ህዝብ አንድ መንግስት
4.       ኢየሩሳሌም እንደገና
5.       ሦስተኛው ቤተ መቅደስ

1.     ድንጋይ በዱንጋይ ላይ ይፈርሳል
ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ። እርሱ ግን መልሶ፦ ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው። ማቴ 241
ንጉስ ሰሎሞን ያሰራው የመጀመርያው የአይሁድ ቤተ መቅደስ በባቢሎን ምርኮ ከፈረሰ ብኃላ ዘሩባበል ሁለተኛውን ቤተ መቅደስ አሳንጾ ነበር:: ጌታ በሚያስተምርበት ወቅት ሄሮድስ ይህንን ቤተ መቅደስ እያሳደሰው ስለነበር በመቅደሱ ግንባታንና በአሰራር ጥበቡ የተደነቁት ሐዋርያት ይህንን አስደናቂ ስራ ጌታ ያየው ዘንድ ስላመቅደሱ ነገሩት፡፡ እርሱ ግን ይፈርሳል አላቸው፡፡ እንደተናገረውም 70 . በሮማዊያን ቤተ መቅደሱ ፈረሰ ጌታም የተናገረው ተፈጸመ ፡፡

እዚህ ጋር የሚነሳው ጥያቄ ይህ ገጸ ምንባብ የተፈጸመ ከሆነ እንዴት ለዘመን ፍጻሜ ምልክት ሊሆን ይችላል የሚለው ነው፡፡ ለዚህ አስረጅ የሚሆንን ሀሳብ እስኪ ከትንቢተ ዳንኤል እንውሰድ፡-

ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል። 
ስለዚህ እወቅ አስተውልም ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።
ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል ጥፋትም ተቀጥሮአል።
ይህ ገጸ ምንባብ 3 የዓመታት ሱባኤዎች የተከፈለ ነው፡፡


1.    62 ሱባኤ  à  አይሁድ ከምርኮ መልስ እንደ መንግስት ለመቆም የሞከሩባቸው 434 ዓመታት በላይ
2.    7   ሱባኤ  à  ኢየሩሳሌምን ለማነጽ የፈጀ 49 ዓመት
3.    1   ሱባኤ   à  3ዓመት 6 ወር የቃል ኪዳን አመታት እና 3ዓመት 6 ወር የታላላቁ መከራ አመታት ናቸው፡፡ 
የሱባኤውን ቁጥር ለመቁጠር ዋና መነሻ ዘመናችን ቅድስቲቱን ከተማ ለማነጽ ትእዛዝ የወጣበት ጊዜ ነው ከተማዋንም ለማነጽ በሶስት የተለያዩ ወቅቶች አዋጅ ተውጆ ነበር፡፡
1.    በቂሮስ ዘመን 538 .              ዕዝ 11-4
2.    በአርጤክስስ ዘመን 458             ዕዝ 712-13
3.    እንደገና በአርጤክስስ ዘመን 445   ነህ 21-8
ብዙ የስነ መለኮት ሊቃውንትና የታረክ ተመራማሪዎች በተለይ የአይሁድ ተሪክ ጸሐፊዎች ለሱባኤው ቁጥር መነሻ ትክክለኛው ጊዜ ሶስተኛው አዋጅ ነው ብለው ይስማማሉ ምክንያቱም፤- በመጀመሪያው ትእዛዝ ቤተ መቅደሱን በዘሩባቤል አማካኘነት ሰሩት እንጅ ገና የከተማዋ ቅጥር አልተቀጠለም ነበር በዚያ ላይ ዘመኑ መሲሁ ከተገደለበት ዘመን አንጻር ልዩነት አለው፡፡ ሁለተኛውም አዋጅ ቢሆን አይሁድ በዕዝራ አመአካኘነት ስለ ታሪካቸውና ባህላቸው ተማሩ እንጅ ያን ያህል ከትንቢቱ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት የለውም፡፡ ከተማይቱ የታነጸችበት እና ቅጥሩም የታጠረበት ዘመን ስለሆነ በተለይም የዘመኑ ቁጥር መሲሁ ከተገደለበት ዘመን ጋር እጅግ ተቀራራቢ በመሆነኑ ሦስተኛው ትእዛዝ የወጣበት ወቅት የሱባኤውን ትክክለኛጊዜ ለማወቅ የተሻለው መነሻ ነው፡፡ ይህ የዳንኤል ትንቢት ጌታ ዓለምን በተቤዠበት ጊዜ በከፊል ተፈጽማል፡፡ እንደተባለውም ዓመጻ ተጨርሳል(ዲያብሎስ ተጣለ) ኃጢአት ተፈጸመ (ፈጽሞ ጠፋ) በደል ተሰረየ (ሁሉ አዲስ ፍጥረት ሆነ) የዘላለም ጽድቅ ገባ (ኢየሱስ ሰው ሆነ) ራዕይና ትንቢት ታተመ (ህግም ነቢያትም ተፈጸሙ) የሚመጣው ህዝብ አለቃም (ሮማዊያን) መቅደሱን አቃጥሎ ከተማዋን አፈረሰ፡፡ ጌታም እንዳለው ድንጋይ በድንጋይ ላይ ፈረሰ፡፡ እንግዲህ የቀረው መሲሁ እስከተገደለበት ያለው ጊዜ 69 ሱባኤ ከሆነ ቀሪዋ 1 ሱባኤስ የሚለው ነው::
……. ………ይቀጥላል

1 comment:

  1. የመምህር በሪሁን ገጽ: ዮሐንስ ራዕይ >>>>> Download Now

    >>>>> Download Full

    የመምህር በሪሁን ገጽ: ዮሐንስ ራዕይ >>>>> Download LINK

    >>>>> Download Now

    የመምህር በሪሁን ገጽ: ዮሐንስ ራዕይ >>>>> Download Full

    >>>>> Download LINK

    ReplyDelete