Tuesday, July 23, 2013

እውነተኛ መምህር

       መምህራን የተማሪወቻቸውን የወደፊት እጣ ፈነታ የመወሰን ሃይል በእጃቸው አለ ተብሎ ይታመናል፡፡ በስርዓተ-ትምህርት ውስጥ ተማሪው ማወቅ ያለበትን ያውቅ ዘንድ ይተጋሉ በብዙ ምሳሌ ነገሩ እስኪገባው ድረስ ለማስረዳት ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን ከነዚህ መምህራን መካከል አንዱም የራሱን ሞት ምሳሌ አድርጎ ያስተመረ የለም ፡፡

መክንያቱም፤-                                            
1.      ወደዚህ ምድር የመጡት ለመሞት ሳይሆን ለመኖር ስለሆነ፡፡
2.     የሚሞቱበትን ሁኔታ እና ጊዜ ስለማያዉቁት ሊሆን ይችላል፡፡
              የጌታ ኢየሱስ አስተምሮ ግን መስቀሉን (ሞቱን) መሰረት ያደረገ ነበር የመጣው ለዚህ ነውና፡፡ ተማሪወቹ ሐዋርያት እርሱ ባለፈበት መንገድ እንዲያልፉ  ፤ እርሱ የደረሰበት ከፍታ እንዲደርሱ …… .በአጠቃላይ እርሱን እንዲመስሉ ያስተምራቸው ነበር፡፡ ለነገሩ ክርስትና ማለት ክርስቶስን መምሰል አይደል፡፡ ክርሰቶስ የሌለው ክርስትና ግልሙትና ነዉ ፡ ፡ክርሰቶስ የሌላትም ቤተ ክርስቲያን ከጣኦት ቤት በምን ትለያለች፡፡

የተጠራነው ለሆሳዕና ዘምረን ለስቅለት ለመበን ሰይሆን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን በትንሳዔው ከብር ከእርሱ ጋር ለመነሳት ነው ሮሜ 65 ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ አልፎ ወደ ተሻለው ለመድረስ ያመነው ስለተአመራቱና ስላበዘው እንጀራ ሳይሆን የህይወታችን አምላክ ስለሆነ መሆኑን አስቀድሞ መረዳት ተገቢ ነው፡፡

           ጌታ ኢየሱስ በቃልና በምሳሌ ካስተማረ ብኃላ ወደ መጨረሻው የትምህርት ክፍለ ጊዜ አለፈ፡፡

ቦታው ፤-  የቀራኒዎ ኮረብታ
ቀን    ፤መጋቢት 27 0033 ዓም ስዓት፤-600-900

          መስቀል በሚባለው ሰሌዳ ላይ እጅግ አስገራሚውን የመጨረሻ ትምህርት አስተማረ፡፡ እግዚአብሔር ካልረዳ በቀር ሰው የማይችላቸውን ፡፡  አስቀድሞ ስጋየን ብሉ ብሎ በቃል ህብስት አበርክቶ በምሳሌ አስተምሮ ነበር አሁን ግን ፍጹም ያደርገዋል ራሱ ተሰውቶ ፤ ጠላቱን ወዶ ፤ የሚወጋውን ፈውሶ ፤ ለሚገሉት እየጸለየ…… እናም የማይጠፋ (expaier) የማያደርግ ፍቅር ፤ ይቅርታ ፤ ትዕግስት…. አስተማረ፡ ፡እውነተኛ መምህር ነውና ሁሉን ሆኖ አስተማረን፡ ፡ክብር ይግባው፡፡  አሜን፡፡ አሜን፡፡ አሜን፡፡    
 
            ጸሎት፤-  አቤቱ አንተ ያጎደለክብን የለም እኛ ግን ብዙ አጉድለናል፡፤ስህተታችን ከምህረተህ አይበልጥምና፤ፍቅርህም ከሀጢያታችን በላይ ስለሆነ፤በደላችን ብዙ ቢሆንም እንካን አባታችን ስለሆንክ፤ንጉሳችን ስለሆነክ፤እረኛችን ስለሆንክ፤፤ይልቁንም ስለምትወደን ማረን አሜን፡፡

No comments:

Post a Comment