Saturday, July 6, 2013

እምነት


እምነት መንገድ ነው መነጽርም ነው መደገፊያ ነው መኖረያም ነው:: ታላቈ የሕይወት ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ እንዳለው የማይታየውን ያሳየናል(እግዚአብሔርን) ተስፍ የምናደርገውን ያስረግጥልናል(ትንሳዔ ሙታንን/መንግስተ ሰማያትን)::ማመን ማለት በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በሚያምኑት እርግጠኛ መሆን ነው::

ለምሳሌ:-  አብርሃም እግዚአብሔርን ከረገጠዉ መሬት በላይ ያምነዉ ነበር፡፡የአብርሃም ታላቅ እምነት እግዚአብሔር ለሙታን ሕይወትን ይሰጣል ብሎ ማመኑ ነዉ፡፡
 
  1. የሞተዉ የሚስቱ የሳራ ገላ ከ75 አመት ብሓላ ትንሳዔ (ልምላመሜ) አግኝቶ ልጅ ልትወልድ ትችላለች ብሎ አመነ ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሙታን ሕይወትን ይሰጣልና ፡፡ሳራ ግን ትስቅ ነበር፡፡
  2.  የሞተ የራሱን ሰዉነት ከ99 ዓመት ብሓላ እንኳን ቢሆን እግዚአብሔር ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም ተብሎ እንደተጻፈ ከዚያ ሁሉ የእርጅና ዘመን በኋላ ተመልሶ ተስፋዉን (ይስሀቅን)እንደሚሰጠዉ የደከመ አካሉ ብርታት አግኝቶ ልጅ አንደሚኖረዉ አመነ፡፡ እግዚአብሔር ለሙታን ሁሉ ሕይወት እንደሚሰጥ ያዉቃልና፡፡ይህ ደግሞ የሀዲስ ኪዳን አምነት ነዉ፡፡ ቅዱስ ጳዉሎስም ወንጌል ለመጀመሪያ ጊዜ ለአብርሃም ተሰበከች እንዳለ፡፡ 
  3. ከሞተዉ ከይስሀቅ ብዙ ዘር ይኖረኛል ብሎ አመነ(ይስሀቅ በአብርሃም ሕሊና ዉስጥ ተሰዉቶ ነበር)፡፡ እግዚአብሔር የተናግረዉን ስለማያስቀር ወይ ይስሃቅ አንዳይሞት ያደርገዋል ወይ ከሞት ይቀሰቅሰዋል ብቻ ይህ የእግዚአብሔር ፈንታ ነዉ እርሱ ግን ከይስሃቅ ሞት ብሓላ የትዉልድ ሀረጉ እንደሚቀጥል አመነ፡፡እምነቱንም በፈተና አሳደገዉ ፡፡
ልጁን ለመሰዋት ሲነሳ በምትኩ ነጭ በግ ተሰጠዉ፡፡ ያም በግ የአለምን ሀጢያት ያስተሰረየዉ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነዉ
  • አብርሃም አንድያ ልጁን ሰጥቶ የእግዚአብሔርን አንድያ ልጅ ተቀበለ፡፡
  • የቤቱን ደስታ ሰጥቶ የአለሙን ደስታ ተቀበለ፡፡
  • በአብርሃም በግ ይስሃቅን አዳነ በእግዚአብሔር በግ አለም ዳነ፡፡ዩሐ 1፡29-30
በዚህም የአብርሃም እምነት ተፈጸመ፡፡ እግዚአብሔርም በአንድያ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለሙታን ሕይወት ሰጠ፡፡  ዩሐ31፡16
ክብር ምስጋና ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ሕያዉ ለሆነዉ፡፡ አሜን፡፡

2 comments:

  1. I Like this page good jobs i Can reed this book
    Dn Berihun Wondwossen (በመምህር በሪሁን)

    ReplyDelete
  2. የመምህር በሪሁን ገጽ: እምነት >>>>> Download Now

    >>>>> Download Full

    የመምህር በሪሁን ገጽ: እምነት >>>>> Download LINK

    >>>>> Download Now

    የመምህር በሪሁን ገጽ: እምነት >>>>> Download Full

    >>>>> Download LINK

    ReplyDelete