Tuesday, July 23, 2013

እውነተኛ መምህር

       መምህራን የተማሪወቻቸውን የወደፊት እጣ ፈነታ የመወሰን ሃይል በእጃቸው አለ ተብሎ ይታመናል፡፡ በስርዓተ-ትምህርት ውስጥ ተማሪው ማወቅ ያለበትን ያውቅ ዘንድ ይተጋሉ በብዙ ምሳሌ ነገሩ እስኪገባው ድረስ ለማስረዳት ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን ከነዚህ መምህራን መካከል አንዱም የራሱን ሞት ምሳሌ አድርጎ ያስተመረ የለም ፡፡

መክንያቱም፤-                                            
1.      ወደዚህ ምድር የመጡት ለመሞት ሳይሆን ለመኖር ስለሆነ፡፡
2.     የሚሞቱበትን ሁኔታ እና ጊዜ ስለማያዉቁት ሊሆን ይችላል፡፡
              የጌታ ኢየሱስ አስተምሮ ግን መስቀሉን (ሞቱን) መሰረት ያደረገ ነበር የመጣው ለዚህ ነውና፡፡ ተማሪወቹ ሐዋርያት እርሱ ባለፈበት መንገድ እንዲያልፉ  ፤ እርሱ የደረሰበት ከፍታ እንዲደርሱ …… .በአጠቃላይ እርሱን እንዲመስሉ ያስተምራቸው ነበር፡፡ ለነገሩ ክርስትና ማለት ክርስቶስን መምሰል አይደል፡፡ ክርሰቶስ የሌለው ክርስትና ግልሙትና ነዉ ፡ ፡ክርሰቶስ የሌላትም ቤተ ክርስቲያን ከጣኦት ቤት በምን ትለያለች፡፡

የተጠራነው ለሆሳዕና ዘምረን ለስቅለት ለመበን ሰይሆን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን በትንሳዔው ከብር ከእርሱ ጋር ለመነሳት ነው ሮሜ 6፤5 ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ አልፎ ወደ ተሻለው ለመድረስ ያመነው ስለተአመራቱና ስላበዘው እንጀራ ሳይሆን የህይወታችን አምላክ ስለሆነ መሆኑን አስቀድሞ መረዳት ተገቢ ነው፡፡

           ጌታ ኢየሱስ በቃልና በምሳሌ ካስተማረ ብኃላ ወደ መጨረሻው የትምህርት ክፍለ ጊዜ አለፈ፡፡

ቦታው ፤-  የቀራኒዎ ኮረብታ
ቀን    ፤-  መጋቢት 27 0033 ዓም ስዓት፤-6፤00-9፤00

          መስቀል በሚባለው ሰሌዳ ላይ እጅግ አስገራሚውን የመጨረሻ ትምህርት አስተማረ፡፡ እግዚአብሔር ካልረዳ በቀር ሰው የማይችላቸውን ፡፡  አስቀድሞ ስጋየን ብሉ ብሎ በቃል ህብስት አበርክቶ በምሳሌ አስተምሮ ነበር አሁን ግን ፍጹም ያደርገዋል ራሱ ተሰውቶ ፤ ጠላቱን ወዶ ፤ የሚወጋውን ፈውሶ ፤ ለሚገሉት እየጸለየ…… እናም የማይጠፋ (expaier) የማያደርግ ፍቅር ፤ ይቅርታ ፤ ትዕግስት…. አስተማረ፡ ፡እውነተኛ መምህር ነውና ሁሉን ሆኖ አስተማረን፡ ፡ክብር ይግባው፡፡  አሜን፡፡ አሜን፡፡ አሜን፡፡    
 
            ጸሎት፤-  አቤቱ አንተ ያጎደለክብን የለም እኛ ግን ብዙ አጉድለናል፡፤ስህተታችን ከምህረተህ አይበልጥምና፤ፍቅርህም ከሀጢያታችን በላይ ስለሆነ፤በደላችን ብዙ ቢሆንም እንካን አባታችን ስለሆንክ፤ንጉሳችን ስለሆነክ፤እረኛችን ስለሆንክ፤፤ይልቁንም ስለምትወደን ማረን አሜን፡፡

ዮሐንስ ራዕይ

                     ክፍል 3

እንዴት ሰነበታችሁ ዘመዶቸ ፡፡ ባለፈው በዘመን ፍጻሜ በእስራኤል ከሚሆኑት ምልክቶች የመጀመሪያውን (ድንጋይ በድንጋይ ላይ ይፈርሳል) ለማየት ሞክረናል ዛሬ ሁለተኛውን እንቀጥላለን :-

2. በለስና ዛፎች

     ምሳሌንም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ በለስንና ዛፎችን ሁሉ እዩ፤ ሲያቈጠቍጡ ተመልክታችሁ በጋ አሁን እንደ ቀረበ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፡፡ ሉቃ21፤29-2

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እስራኤል በአብዛኛው በሶስት ዛፎች ተወክላ እናገኛታለን ፤- በበለስ ፤ በወይራ እና በወይን ሆሴ 9፤10 ሮሜ 11፤17 ኢሳ 5፤1 ኢዩ 1፤7 የኛ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም በለስ ዘይቤ ቤተ እስራኤል እሙንቱ (በበለስ የተመሰለው የእስራኤል ቤት ነው) ብለው ተርጉመውታል፡፡

በእስራኤል የበለስ ቅጠል ሲለሰልስ ክረምቱ አልፎ በጋ እየቀረበ እንደሆነ አመላካች እንደሆነው ሁሉ በበለስ የተመሰለችው እስራኤል ስታቆጠቁጥ (እንደገና እንደ ሀገር ስትመሰረት) ዛፎችም እንዲሁ መብቀል ሲጀምሩ (ሌሎች መንግስታትም ነጻነታቸውን ሲቀዳጁ)

በጋ የተባለው የጌታ ዳግም ምጽአት እጅግ ቅርብ ይሆናል፡፡
አብዛኛወቹ የስነ-መለኮት ሊቃውንተና የትንቢት ተመራማረወች እንደሚስማሙበት ይህ የጌታ ኢየሱስ ትንቢት እስራኤል እንደገና በተመሰረተችበትና ብዙ ሀገሮች ነጻ በወጡበት በዚህ እኛባለንበት በ 20ኛው ክፍለ ዘመን ተፈጽሟል፡፡

·         በለሷ (እስራኤል) በ 1948 እ.ኤ.አ ስለተመሰረተች(ከፈረሰች ከ 2553 አመት ብኃላ)፤- ይህንን ሃሳብ በሚቀጥለው ክፍል እንደገና በሰፊው እንመለስበታለን፡፡

·         ዛፎች (ነጻ መንገስታት) በ 1945 የተባበሩት መንግስታት በ 51 ልኣላዊ ሀገራት ስለተመሰረተ፡፡ አሁን ከ200 ሀገራት በላይ በአባለነት ይዛል፡፡

እነዚህ ሁለት የታሪክ ክስተቶች ለጌታ ዳግም ምጽአት እጅግ መቅረብ እንደ ሁነኛ ማሳያወች ከማገልገላቸውም በላይ አሁን ባለንበት በአንዱ ቀን እንኳን ጌታ ሊመጣ ይችላል ብለን እንድናስብ የሚያስገድዱ ግልጽ ምልክቶች ናቸው፡፡

ዋናው ነገር ቀኑም ሆነ ስአቱ ስለማይታወቅ ተዘጋጅቶ መጠበቅ ነው፡፡

ንስሀ ገብተን ስጋ ወደሙ ተቀብለን ተዘጋጅተን ጌታን በአየራት ለመቀበል ያብቃን ፡፡

                    አሜን::::::

Monday, July 15, 2013

ዮሐንስ ራዕይ

ክፍል ሁለት

ይሄው ዓለምም ሳትጠፋ የፈረንጆቹ Dec 21-2012 አለፈ፡፡ እግዚአብሔርም ዘመን ለንስሀ ጨመረልንና እንደገና ተገናኘን እንዴት ሰነበታችሁ ዘመዶቸ፤፤ወደፊት በዝርዘር የምንመጣበት ቢሆንም ከዓለም ጥፋት ጋር ተያይዞ አንድ ሁለት ነገሮችን ጠቆም ላድርግና ወደዛሬው ክፍል ልለፍ፡፡
1.      ከዓለም ጥፋት በፊት አውሬው (የጥፋት ልጅ) በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ይቀመጣል:: ይህ ማለት ደግሞ እስራኤል 3ኛውን    ቤተ መቅደስ ሳትስራ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት አይሆንም ማለት ነው፡፡
2.      ከዚህ በፊት ዓለም ጠፍቶ ያውቃል (በኖህ ዘመን) ታዲያ ያኔ እግዚአብሔር ምርጦቹን ከጥፋት ከለላቸው፡፡ ስለዚህ ዓለም ቢያልፍም ባያልፍም ፤ በማነኛውም ጊዜ እና ሁኔታ እግዚአብሔር ልጆቹን ይጠብቃል::
አሁን ደግሞ ወደ ዛሬው ትምህርታችን እንመለስ
ስለ ፍጻሜ ዘመን ስናስብ በቅድስቲቱ ከተማ በተቀደሰው ቤተ መቅደስ በቅዱሱ ህዝብ በአጠቃላይ በቅድስት ሀገር የሚከሰቱት ኩነቶች እጅግ ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ወሳኘ ጉዳዮች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ጌታም እንደተናገረው እነዚህ ነገሮች በስስራኤል ይሆናሉ :-
1.       ድንጋይ በዱንጋይ ላይ ይፈርሳል
2.       በለሷ ትለመልማለች
3.       አንድ ህዝብ አንድ መንግስት
4.       ኢየሩሳሌም እንደገና
5.       ሦስተኛው ቤተ መቅደስ

Monday, July 8, 2013

ዮሐንስ ራዕይ

እንደ መግቢያ፤-

አንዳንድ ሊቃውንት ዮሐንስ ራዕይ የሚተረጎመው ዘመኑ ሲደርስ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ የለም ጌታ ሁሉን ነግሮናል መንፈስ ቅዱስን አጋዥ አድርገን እንተረጉመዋለን ይላሉ፡፡የተቀሩት ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ አስተማሪነት እንዳለ ሆኖ ዘመን የሚገልጠው ነገር አለ ፤ በተፈሮ ሁኔታ የሚፈታ አለ፤በዓለም ተለዋወጭ ሁኔታ(በሳይንስና ቴክኖሎጅ ፤ በስነ-ምግባርና በሞራል ጉዳዮች…..) እና በአጠቃላይ ከዕለት ዕለት የሰው ልጅ እንቃስቃሴ ጋር ተያይዞ የሚተረጎም አለ ይላሉ፡፡ የሆነ ሆኖ እኛ ግን የቆየውን የኢትዮጵያ ሊቃውንት አስተምህሮ እየተከተልን ነገሩን ለመመርመር እንሞክራለን፡፡

ጌታችን ሁሉን ከፈጸመ ብኃላ አጽናኙን አንደሚልክላቸው ለሐዋርያቱ ቃል ገብቶ የነፋስ መሰላል የአየር መወጣጫ ሰርቶ ደመናውን እየረገጠ ወደ ሰማይ ወጣ፡፡ በጊዜው የነበሩት መላእከት ደገሞ የመንፈስ ቀዱስ መውረድ በቻ ሳይሆን ኢየሱስም ተመልሶ እንደሚመጣ አበሰራቸው፡፡ ደስታቸውም እጽፍ ድርብ ሆነ፡: በዚህም እሰከ ዓለም ፍጻሜ ከእናንተ ጋር ነኘ ያለው የመጽሐፍ ቃል ተፈጸመ፡፡

በሃይማኖት ስንኖር ነፍሳችንን አስይዘን ቢሆን ከምንወራረድባቸው ጉዳች አንዱ የጌታ ዳግም ምጽአት ነው፡፡ በእርግጥ ጌታ ይመጣል፡፡ አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል።  አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና   ራዕ 22፤20 በሌሎች ገጸ-ምንባባትም እንዲህ ተጽፎል:-

የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤ መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ። ማቴ 24፤30-31

እግዚአብሔር እንዴህ ይላል በጫንቃ ላይ ይሸከሙአችኋል በጕልበትም ላይ እያስቀመጡ ያቀማጥሉአችኋል።
እናት ልጅዋን እንደምታጽናና እንዲሁ አጽናናችኋለሁ፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ትጽናናላችሁ  ኢሳ 66፤12-13


ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ። ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤ ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው። የሐ 1፤8-11

     ሊሆን ያለውን ሁሉ ግን ጌታ ኢየሱስ አስቀድሞ በማቴዎስ ወንጌል 24፤1-ፍም እንደተጻፈው በዝርዘር ከነምሳሌውና ምልክቱ ገልጦላቸዋል፡፡ ይህ ክፍል ለዮሐንስ ራዕይ እንደመግቢያ ነው ብየ አስባለሁ ወይም ዮሐንስ ራዕይ የዚህ ክፍል ዝርዘር ትርጉም ነው እንደማለት ነው፡፡ ነገረ ምጽዐትን የሚተርከውን ይህንን ምዕራፍ በአራት ዓበይት ክፍሎች ልንከፍለው እንችላለን፡፡

1.    በእስራኤል የሚከሰቱ ሁኔታወች
2.    በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚፈጠሩ ነገሮች
3.    ተፈጥሮዊ ኩነቶች
4.    ሃይማኖተዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡

………. ይቀጥላል………